エピソード

  • የግንቦት 22 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/05/30
    ከአዲስ አበባና ከሌሎች የመሐል ኢትዮጵያ ግዛቶች ሸቀጦች ጭነዉ ወደ ትግራይ ይጓዙ የነበሩ የጭነት መኪኖች አፋርና አማራ ክልል በሚገኙ የፍተሻ ጣቢያዎች መታገዳቸዉን ሾፌሮች አስታወቁ።---የአሜሪካዉ አዉሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ኢንዶኔዢያና ኢትዮጵያ ዉስጥ በደረሱ አደጋዎች ሰበብ የተመሠረተበት ክስ ሊነሳለት ነዉ።ክሱ የሚነሳዉ ቦይንግ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል በመስማማቱ ነዉ።-እስራኤል ለጋዛ ሕዝብ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይደርስ ማገዷን እንድታቆም የሚደረግባት ግፊት እንደቀጠለ ነዉ።የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ግን መንግሥታቸዉ ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የአይሁዳዊ የእስራኤል መንግሥት እንደሚመሠርት ዝተዋል።
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • የግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    2025/05/29
    *የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢሳያስ አፈወርቂ ወቀሳ ላይ ምላሽ ሰጠ *የግብፁ ፕሬዚዳንት አልሲሲ ብርቱ ተፎካካሪ ከስር ተፈቱ * ናይጄሪያ ውስጥ በሁለት አመታት ውስጥ ከ 10 000 በላይ ሰዎች ተገደሉ *«እስራኤል በጋዛ የጦር ወንጀል እየፈፀመች ነው» የቀድሞ የእስራኤል ጠ/ሚነስትር *ኤሎን ማስክ ለትራምፕ መስራታቸውን ሊያቆሙ ነው *የዩናይትድ ስቴትስ ለአለም አቀፍ ተማሪዎች ቪዛ ላለመስጠት መወሰኗ ቁጣ ቀሰቀሰ
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2025/05/28
    የደርግ ሥርዓት ከኢትዮጵያ የመንግሥት ሥልጣን ከተወገደ ዛሬ 34 ዓመቱን ደፈነ። ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በብሔራዊ በዓልነት ይታሰብ የነበረው ግንቦት 20 በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች መደበኛ የሥራ ቀን ሆኖ ሲያልፍ ትግራይ ክልል ግን በደመቀ ሥርዓት ተከብሯል። ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በሱዳን ጦር ኃይል የተያዙ አካባቢዎች ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙ ተዘገበ። የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቁ። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአብዛኛው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናትን ጨምሮ ወደ 300 ገደማ ህሙማን ላይ በደል በፈጸመ የቀዶ ህክምና ባለሙያ ላይ የ20 ዓመት እስራት ፈረደ።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 19 ቀን 2017
    2025/05/27
    አርስተ ዜና በእነአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ የተሰኘ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ግዚያዊ የምዝገባ ፍቃድ አገኘ።--በጦርነት በተመሰቃቀለችዉ ሱዳን በኮሌራ በሽታ የተያዘዉ ሰዉ ቁጥር መጨመሩን የጤና ጥበቃ ሚ/ር አስታወቀ።--የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ፍሬድሪክ ሜርስ ስራኤል በጋዛ እየፈፀመች ያለዉ ድርጊት «ትክክል ያልሆነ» ሲሉ ወቀሱ። በሌላ በኩል ጀርመንን ጨምሮ ቁልፍ ምዕራባዉያን የዩክሪን ደጋፊዎች ለዩክሪን በሚልኩት የጦር መሳርያ ላይ የተጣለ ገደብን አነሱ።--የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የፊንላንድ የአየር ክልልን ጥሰዋል ከተባለ በኋላ ፊንላንድ የሩሲያን አምባሳደር ለጥያቄ ጠራች።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2025/05/26
    በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ አውቶብስ ላይ ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ስድስት ሰዎችም ተጎድተዋል። ጥቃት አድራሾቹ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች መሆናቸው ተገልጿል። የግሪክ ባሕር ኃይል ከ500 በላይ ስደተኞችን ከመስመጥ ማዳኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ። ዩጋንዳ ከጀርመን ጋር መከላከያን በተመለከተ ያላትን ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች። የእስራኤል መንግሥት በቅርቡ ጋዛ ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነገረ። ሃገራት እስራኤል ጋዛ ላይ የምትወስደውን የኃይል እርምጃ እንድታቆም እየጠየቁ ነው።
    続きを読む 一部表示
    8 分
  • DW Amharic የግንቦት 17 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/05/25
    በኢትዮጵያ “ኤምፖክስ” ተብሎ በሚጠራው የጦጣ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ መንግሥት እና ሕዝብ ለኢትዮጵያ “ተሐድሶ ወይም ለውጥ በከፍተኛ ተስፋ ባደረጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ ድንገት በተፈጠሩ ክስተቶች ምክንያት እንደማይቆጩ” ተናገሩ። በጋዛ በአንድ ቀን 38 ሰዎች በእስራኤል ጥቃቶች መገደላቸውን የሐማስ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሩሲያ እና ዩክሬን በሦስት ዙር ያካሔዱትን የጦር ምርኮኞች ልውውጥ አጠናቀቁ። የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዶብሪንት የተወሰኑ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን ወደ ጀርመን ከማምጣት የሚከለክል ሕግ እየተዘጋጀ መሆኑን አረጋገጡ።
    続きを読む 一部表示
    9 分
  • DW Amharic የግንቦት 16 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/05/24
    አፍሪካ በማዕድናት፣ በሚታረስ መሬት እና በኢንዱስትሪ ያላትን እምቅ ሀብት ለዛሬውም ሆነ ለወደፊቱ ትውልድ ሲባል መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር አሳሰቡ። ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ በሚያዝያ 2018 በሚካሔደው የጅቡቲ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ በገደምዳሜ ፍንጭ ሰጡ። በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ማኪና በተባለ አካባቢ በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ የ79 ሰዎች አስከሬኖች ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ሆስፒታሎች መድረሳቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
    続きを読む 一部表示
    9 分
  • የዐርብ ግንቦት 15፣ ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
    2025/05/23
    ቤኒሻንጉል፥ በካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ የታጣቂዎች ጥቃት፤ ለንደን፥ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፦ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከጤና ባለሞያዎች ጋር በአሰቸኳይ ሊነጋገሩ ይገባል አለ፤ አአ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡን እየጎዳ ላለው ግጭት መፍትሄ እንዲፈለግ አሳሰበች፤ ጋምቤላ፥ ኢትዮጵያ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች «የጤና ቀውስ» የማይቀር ነው ተባለ፤ ዋሽንግተን፥ ትራምፕ የአውሮጳ ኅብረት ሸቀጦች ላይ የ50 በመቶ ቀረጥ ሊጥል ነው፤ ዩክሬን እና ሩስያ ከዚህ ቀደሙ ከፍተኛ የሆነ የእስረኛ ልውውጥ አደረጉ ።
    続きを読む 一部表示
    10 分