『የዓለም ዜና』のカバーアート

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

著者: DW
無料で聴く

このコンテンツについて

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2025 DW 政治・政府
エピソード
  • የግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2025/05/28
    የደርግ ሥርዓት ከኢትዮጵያ የመንግሥት ሥልጣን ከተወገደ ዛሬ 34 ዓመቱን ደፈነ። ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በብሔራዊ በዓልነት ይታሰብ የነበረው ግንቦት 20 በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች መደበኛ የሥራ ቀን ሆኖ ሲያልፍ ትግራይ ክልል ግን በደመቀ ሥርዓት ተከብሯል። ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በሱዳን ጦር ኃይል የተያዙ አካባቢዎች ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙ ተዘገበ። የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ዩናይትድ ስቴትስን አስጠነቀቁ። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአብዛኛው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናትን ጨምሮ ወደ 300 ገደማ ህሙማን ላይ በደል በፈጸመ የቀዶ ህክምና ባለሙያ ላይ የ20 ዓመት እስራት ፈረደ።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 19 ቀን 2017
    2025/05/27
    አርስተ ዜና በእነአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ የተሰኘ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ግዚያዊ የምዝገባ ፍቃድ አገኘ።--በጦርነት በተመሰቃቀለችዉ ሱዳን በኮሌራ በሽታ የተያዘዉ ሰዉ ቁጥር መጨመሩን የጤና ጥበቃ ሚ/ር አስታወቀ።--የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ፍሬድሪክ ሜርስ ስራኤል በጋዛ እየፈፀመች ያለዉ ድርጊት «ትክክል ያልሆነ» ሲሉ ወቀሱ። በሌላ በኩል ጀርመንን ጨምሮ ቁልፍ ምዕራባዉያን የዩክሪን ደጋፊዎች ለዩክሪን በሚልኩት የጦር መሳርያ ላይ የተጣለ ገደብን አነሱ።--የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የፊንላንድ የአየር ክልልን ጥሰዋል ከተባለ በኋላ ፊንላንድ የሩሲያን አምባሳደር ለጥያቄ ጠራች።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2025/05/26
    በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ አውቶብስ ላይ ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ስድስት ሰዎችም ተጎድተዋል። ጥቃት አድራሾቹ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች መሆናቸው ተገልጿል። የግሪክ ባሕር ኃይል ከ500 በላይ ስደተኞችን ከመስመጥ ማዳኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ። ዩጋንዳ ከጀርመን ጋር መከላከያን በተመለከተ ያላትን ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች። የእስራኤል መንግሥት በቅርቡ ጋዛ ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነገረ። ሃገራት እስራኤል ጋዛ ላይ የምትወስደውን የኃይል እርምጃ እንድታቆም እየጠየቁ ነው።
    続きを読む 一部表示
    8 分

የዓለም ዜናに寄せられたリスナーの声

カスタマーレビュー:以下のタブを選択することで、他のサイトのレビューをご覧になれます。