『ማሕደረ ዜና』のカバーアート

ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና

著者: DW
無料で聴く

このコンテンツについて

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ2025 DW 政治・政府 政治学 社会科学
エピソード
  • የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትችትና ነቀፋ የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን?
    2025/05/26
    ፐሬዝደንት ኢሳያስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወይም ባካባቢዉ የታወጀ ጦርነት አንድ አይደለም። «ብዙ ጦርነቶችን ለማስቀጠል ዘመናይ ቴክኖሎጂና ጦር መሳሪያ እየተሰበሰበ ነዉ» ብለዋል።የብልፅግና ፓርቲ ለቴክኖሎጂና ለጦር መሳሪያ የሚያወጣዉ ዶላርም ልክ የለዉም ብለዋል።ኢሳያስ «ርካሽ» ያሉት ፉከራና ቀረርቶ በእሳቸወ አገላለፅ ተመዝግቧል።«የኤርትራን ሕዝብና መንግሥትን ወደ ግጭት ለማስገባት የሚሸረበዉ ግልፅና ሥዉር ሴራን ያላወቀዉ የለም» ይላሉ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት።የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን?
    続きを読む 一部表示
    15 分
  • ማሕደረ ዜና፣ ሕንድና ፓኪስታን የዝንተ ዓለም ጠላቶች
    2025/05/12
    የሒንዱ፣የሲክና የቡዳሐ አማኞች በብዛት የሚኖሩበት ግዛት ሕንድ ሲባል፣ ሙስሊሞች የሚበዙበት የዛሬዎቹ ፓኪስታንና ባንግላዴሽ ግዛቶች ደግሞ ፓኪስታን ሆኑ።ክፍፍሉ ሲደረግ ሙስሊሞች በብዛት የሚኖሩበት የጃሙ ካሽሚር ካሽሚር ግዛት ግን የሒንዱ እምነት የሚከተሉት የግዛቱ አገረ-ገዢ እንደጠየቁት ነፃ መንግስትም ሳይሆን፣ ከፓኪስታንና ሕንድም ሳይጠቃለል ለወደፊቱ ግጭት እንዲመች ተንጠልጥሎ ቀረ።
    続きを読む 一部表示
    14 分
  • ማሕደረ ዜና፣ የፕሬዝደንት ትራምፕ ሠላም የማስፈን ቃልና ተቃራኒ ርምጃ
    2025/05/05
    በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ደግሞ የእስራኤል ጦር ገና በቅጡ ያልጠናዉን የሶሪያ መንግስት ይዞታዎችን በተዋጊ ጄቶች ደብድቧል።እስራኤል ጋዛን፣ ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ዳርቻን ፣የመንን፣ ኢራንን፣ ሊባኖስን መናደፏ አልበቃ ብሏት በተለያዩ የሶሪያ ጎሳ ወይም የሐይማኖት ሐራጥቃ ተከታዮች መካከል በተነሳ ጠብ ጣልቃ ገብታ በ14 ዓመት ጦርነት የወደመችዉን ሶሪያን ደጋግማ መደብደቧ ለብዙ ታዛቢ ግራ አጋቢ ነዉ።ሶሪያዊ አዛዉንት እንደሚሉት ግን የእስራኤል ጥቃት በአረብ መሪዎች ዝምታ፤ በዶንልድ ትራምፕ ይሁንታ የታገዘ ነዉ።
    続きを読む 一部表示
    13 分

ማሕደረ ዜናに寄せられたリスナーの声

カスタマーレビュー:以下のタブを選択することで、他のサイトのレビューをご覧になれます。